Fana: At a Speed of Life!

ለሸኔ የሽብር ቡድን የትጥቅ ድጋፍ ለማድረግ ሲጓዙ ነበር የተባሉ 2 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ለሸኔ የሽብር ቡድን የትጥቅ ድጋፍ ለማድረግ ሲጓዙ ነበር የተባሉ ሁለት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታውቋል።

ተጠርጣሪዎቹ ሰኔ 20 ቀን 2015 ዓ.ም መነሻቸውን ከአዲስ አበባ ከተማ ለቡ አድርገው አንድ ብሬን እና 263 የክላሽንኮቭ ጠመንጃ ጥይቶችን ጭነው ሲጓዙ ሆለታ ከተማን እንዳለፉ ነው በቁጥጥር ሥር የዋሉት፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ከህገ-ወጥ የጦር መሣሪያው በተጨማሪ ለእኩይ ዓለማቸው ማስፈፀሚያ ሐሰተኛ የአዲስ አበባ ከተማ የነዋሪ መታወቂያ፣ የልደት ምስክር ወረቀት፣ ልዩ ልዩ ማህተሞች እና ሀሰተኛ ሰነዶችን እንደያዙ በቁጥር ሥር ውለው ጉዳያቸው በምርመራ እየተጣራ እንደሚገኝ ተጠቁሟል፡፡

ተጠርጣዎቹ በፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል በተደረገ ጠንካራ ክትትል በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የፌደራል ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡

ኅብረተሰቡም እነዚህ ህገወጥ መሣሪያዎች በሸኔ የሽብር ቡድን እጅ ቢገቡ ኖሮ በንፁሃን ዜጎቻችን ላይ የሚያደርሱት ከፍተኛ መሆኑን ተገንዝቦ መሰል የወንጀል ተግባራትን ሲመለከት ለፀጥታ አካላት በፍጥነት ጥቆማ በመስጠት እያደረገ ያለውን ተሳትፎ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ቀርቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.