የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በጅማ ከተማ ተከበረ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 1 ሺህ 444ኛው የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በጅማ ከተማ ተከብሯል፡፡
በዓሉ በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስነ-ስርዓቶች ነው የተከበረው፡፡
በአከባበር ስነ-ስርዓቱ ሰላት እና ተክቢራን ጨምሮ የተለያዩ ሃይማኖታዊ ስነ-ስርዓቶች ተከናውነዋል፡፡
በተመሳሳይ የአረፋ በዓል በአሰላ ፣ ነቀምቴ እና ሌሎች ከተሞች በተለያዩ ስነ ስርዓቶች ተከብሯል፡፡
በአብዱረህማን መሃመድ