Fana: At a Speed of Life!

በጋምቤላ የሚከሰት የሰላም መደፍረስን ለመከላከል በትኩረት እንዲሠራ ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ በክልሉ እየተከሰቱ ያሉ የሰላም መደፍረሶችን ለመከላከል በትኩረት መስራት እንደሚገባ አሳሰቡ፡፡

አቶ ኡሞድ ኡጁሉን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በጋምቤላ ከተማ ክልል አቀፍ ሕዝባዊ የሰላም ጉባዔ እየተካሄደ ነው፡፡

ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ በጉባዔው ላይ በክልሉ እየተከሰቱ ያሉ የሰላም መደፍረሶችን ለመከላከል በትኩረት መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

በተለይም የሀገር ሽማግሌዎችና የሐይማኖት አባቶች ሚና ላቅ ያለ ነው ማለታቸውን የክልሉ ፕሬስ ሴክሬታሪያት መረጃ ያመላክታል፡፡

በአንዳንድ የክልሉ አካባቢዎች የሚስተዋሉ አለመግባባቶችን በሰላም ለመፍታት የሚያስችሉ አቅጣጫዎችን በጉባዔው ላይ እንደሚያስቀምጡም አንስተዋል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.