ኢትዮጵያ እና ጀርመን የ1 ነጥብ 25 ቢሊየን ብር የድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ጀርመን የ1 ነጥብ 25 ቢሊየን ብር የድጋፍ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡
ድጋፉ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ንግድ ኢንሹራንስ ኤጀንሲ (ኤ ቲ አይ) የምታደርገውን አስተዋፅዖ ለማሳደግ እንደሚያስችል ተገልጿል፡፡
የተደረገው ድጋፍ ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2030 መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ለመሰለፍ የምታደረገውን ጥረት ለማሳካት ያለመ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡
በተመሳሳይ ኢትዮጵያ እና የዴንማርክ መንግስት የ555 ሚሊየን ብር የድጋፍ ስምምነት መፈራረማቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
የድጋፍ ስምምቱን የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው ከሀገራቱ መንግስታት ተወካዮች ጋር ተፈራርመዋል፡፡