ስፓርት

በሪሁ አረጋዊ በሉዛን ዳይመንድ ሊግ በ5 ሺህ ሜትር የአመቱን ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ አሸነፈ

By Mekoya Hailemariam

July 01, 2023

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያዊው አትሌት በሪሁ አረጋዊ በሉዛን ዳይመንድ ሊግ በወንዶች 5 ሺህ ሜትር ድል ቀንቶታል።

አትሌት በሪሁ ርቀቱን 12:40:45 በሆነ ጊዜ አጠናቆ የአመቱን ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ አሸንፏል።

በርቀቱ የሪከርዱ ባለቤት የነበረው ጆሹዋ ቸፕቴጌ 2ኛ ወጥቷል።

የሃገሩ ልጆች ሃጎስ ገ/ህይወት 3ኛ፣ ጥላሁን ኃይሌ 4ኛ፣ ሰለሞን ባረጋ 5ኛ፣ ኩማ ግርማ 7ኛ፣ ገመቹ ዲዳ 8ኛ ሆነዋል።

በሴቶች መካከል በተካሄደው የ3 ሺህ ሜትር መሠናክል ውድድር ኢትዮጵያዊቷ ሲምቦ አለማየሁ 2ኛ ስትሆን ዘርፌ ወንድማገኝ 4ኛ፣ ሎሚ ሙለታ 5ኛ፣ መቅደስ አበበ ደግሞ 11ኛ ሆነው ማጠናቀቃቸውን ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።