በኢትዮጵያ በ24 ሰዓት ውስጥ ለ1 ሺህ 408 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ምርመራ ተደረገ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 22፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ባለፉት በ24 ሰዓታት ውስጥ ለ1 ሺህ 408 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ምርመራ መደረጉን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለፁ።
ባለፉት በ24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ ምርመራም ተጨማሪ 1 ሰው ላይ የኮሮና ቫይረስ መገኘቱንም ሚኒስትሯ አስታውቀዋል።
ቫይረሱ የተገኘባቸው ግለሰብ ኢትዮጵያዊ ሴት ሲሆኑ፥ ነዋሪነታቸው በባህር ዳር ከተማ መሆኑን እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው እንደሆነም ገልፀዋል።
ይህንን ተከትሎም በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 131 መድረሱንም ነው ዶክተር ሊያ ያስታወቁት።
ዶክተር ሊያ አክለውም በ24 ሰዓት ውስጥ ተጨማሪ አንድ ሰው ከቫይረሱ ማገገሙን አስታውቀው፤ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 59 መድረሱንም ገልፀዋል።
በአጠቃላይ በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 131 ሲሆን፥ ከእነዚህም ውስጥ 67 ሰዎች በለይቶ ህክምና ላይ፤ 59 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ አገግመዋል።
በቫይረሱ የ3 ሰዎች ህይወት ማለፉ የሚታወስ ሲሆን፥ ሁለት ሰዎች ደግሞ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ መደረጉ አይዘነጋም።
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።