ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ በይርጋዓለም ከተማ የተገነቡ ሶስት ፕሮጀክቶችን መርቀው ከፈቱ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲፈዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ በማዕከላዊ ሲዳማ ዞን በይርጋዓለም ከተማ የተገነቡ ሶስት ፕሮጀክቶችን መርቀው ከፈቱ፡፡
ፕሮጀክቶቱ የመንገድ፣የድልድይ እና የገበያ ማዕከል ሲሆኑ÷ የህዝብን ጥያቄ መሰረት አድርገው የተገነቡ መሆናቸውን ከሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡