Fana: At a Speed of Life!

በሰሜን ሸዋ ዞን በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ3 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ሣማ ቀበሌ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሶስት ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡

አደጋው ከአዳማ ወደ አረርቲ ሠዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ አነስተኛ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ በመገልበጡ ነው የደረሰው።

በአደጋው ለህልፈት ከተዳረጉት በተጨማሪም 12 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላልጉዳት መድረሱ ተገልጿል።

ተጎጂዎች በአረርቲ ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገላቸው እንደሚገኙም የአማራ ክልል ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡

ለአደጋው መከሰት መንስኤ ከመጠን በላይ ፍጥነት  እንደነበር የተገለጸ ሲሆን÷ ከትራፊክ አደጋ መጠንቀቅ እንደሚገባም ፖሊስ መልዕክት አስተላልፏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.