ስፓርት

በስቶኮልም በተካሄደው ዳይመንድ ሊግ ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች አሸነፉ

By Feven Bishaw

July 03, 2023

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሲዊዲን ስቶኮልም በተካሄደው ዳይመንድ ሊግ ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በተለያዩ ርቀቶች ድል ቀንቷቸዋል።

የ2023 የዳይመንድ ሊግ 7ኛው ዙር ውድድር በስቶኮልም የተካሄደ ሲሆን በ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች ውድድር ኢትዮጵያዊን አትሌቶች ተከታተለው በመግባት አሸንፈዋል።

በዚህ የ1 ሺህ 500 ሜትር የሴቶች ውድድር አትሌት ፍሬወይኒ ሃይሉ በአንደኝነት አጠናቃለች።

እንዲሁም አትሌት ድርቤ ወልተጂ ሁለተኛ፤ ሂሩት መሸሻ ደግሞ የሶስተኝነት ደረጃ በመያዝ አጠናቅቀዋል፡፡