Fana: At a Speed of Life!

እስራኤል በዌስት ባንክ  ጀኒን ከተማ ላይ ጥቃት ፈፀመች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) እስራኤል  በዌስት ባንክ በሚገኘው የፍልስጤማውያን መጠለያ ካምፕ ላይ የአየር ጥቃት መፈፀሟን አስታውቃለች፡፡

የእስራኤል ጦር ዌስት ባንክ ሰሜናዊ ክፍል በሚገኘው  ጄኒን ከተማ ላይ ከፍተኛ ወታደራዊ ዘመቻ መጀመሯ ተሰምቷል።

የፍልስጤም ጤና ሚኒስቴር ለቢቢሲ እንደተናገሩት፥ እስራኤል በፈፀመችው የድሮን ጥቃት ሶስት ሰዎች ሲሞቱ ከ20 የሚበልጡ ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን ገልፀዋል፡፡

የእስራኤል መከላከያ ሰራዊት በበኩሉ÷ በጄኒን  የመጠለያ ካምፕ ውስጥ የሰፈረውን የሽብር ቡድን መሰረተ ልማቶች በመለየት እየመታ መሆኑን ነው ያስታወቀው፡፡

አሸባሪዎች ጄኒን ካምፕን እንደ መሸሸጊያ ተጠቅመው በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጉዳት ሲያደርሱ ዝም ብለን አንመለከትም ያለው የእስራኤል ጦር “ካምፑ የአሸባሪዎች መሸሸጊያ ነው” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ፋታህ፣ ሃማስ እና እስላሚክ ጂሃድ በመባል የሚታወቁትን የፍልስጤም ተዋጊዎች በአንድነት ያቀፈው እና ጀኒን ባታሊዮን በመባል የሚጣወቀው የፍልስጤም ጦር “የእስራኤል ወራሪ ሀይሎችን እስከመጨረሻው እስትንፋስ እንዋጋቸዋለን” ሲል አስታውቋል፡፡

በባለፈው ወር  እስራኤል ጀኒን በተባለው የፍልስጤም ካምፕ ላይ በፈፀመችው የአየር ጥቃት ስድስት ፍልስጤማውያን  መግደሏን ቢቢሲ በዘገባው አስታውሷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.