ስፓርት

የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኮከብ ተጫዋች እጩዎች ይፋ ሆኑ

By Mikias Ayele

July 03, 2023

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2015 ዓ.ም የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኮከብ ተጨዋች እጩዎች ይፋ ሆነዋል።

በዚህ መሰረትም ቢኒያም በላይ እና እስማኤል ኦሮ አጎሮ ከቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ፉዓድ ፈረጃ ፣ያሬድ ባየህና  አለልኝ አዘነ ከባህር ዳር ከተማ፣ ባሲሩ ኡመር ከኢትዮጵያ መድኀን እንዲሁም ጌታነህ ከበደ  ከወልቂጤ ከተማ በእጩነት ቀርበዋል፡፡

በምርጥ በረኛ እጩ ዝርዝር ደግሞ አቦበከር ኑራ ከኢትዮጵያ መድን፣ ፔፔ ሳይዶ ከሀድያ ሆሳዕና እንዲሁም ቢኒያም ገነቱ ከወላይታ ድቻ በእጩነት መቅረባቸውን የሊግ ኩባንያው መረጃ  ያመላክታል፡፡

ስለሆነም የስፖርት ቤተሰቡ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ምርጫን እስከ ሰኔ 29 ቀን 2015 ዓ.ም እንዲያከናውን ጥሪ ቀርቧል፡፡