Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባላት በከተማዋ የተከናወኑ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባላት እየተጠናቀቀ ባለው የበጀት ዓመት በመዲናዋ የተከናወኑ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝታቸውም÷ በከተማ አስተዳደሩ እየተከናወኑ ያሉ ሰው ተኮር  የልማት ሥራዎች፣ የቤቶች ዕድሳትና ግንባታ፣ የከተማ ግብርና ፣ የሌማት ትሩፋት የእስሳት እርባታ እና የንብ ማነብ ተግበራትን ተመልክተዋል፡፡

በተጨማሪም በ90 ቀናት የተገነባው የእንጀራ መጋገሪያ ፋብሪካ፣ የመሸጫ ሼዶች ልማትና ስርጭት እንዲሁም የወጣቶች ስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ግንባታ እና የተማሪዎች መመገቢያ ማዕከላትን ጎብኝተዋል፡፡

በከተማ አስተዳደሩ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች ውጤት የታየባቸው መሆናቸውንም ነው ጎብኝዎቹ የገለጹት፡፡

ይህ ትግባር በሚቀጥለው በጀት ዓመትም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ማለታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.