ጠ/ሚ ዐቢይ በአርባምንጭ ከባይራ ልዩ አዳሪ ት/ቤት ተማሪዎች ጋር ችግኝ ተከሉ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአርባምንጭ ከተማ ከባይራ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ጋር ችግኝ ተክለዋል፡፡
በሌላ በኩል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው ዕለት ለአርባ ምንጭ ኮንፈረንስ ሪዞርት ግንባታ የመሠረት ድንጋይ አስቀምጠዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ ‘የሸገር’እና ‘ገበታ ለሀገር’ የቱሪዝም ዘርፍ የልማት ሥራዎች በአብዛኛው ተጠናቅቀዋል ብለዋል።