የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ2016 ረቂቅ በጀት ላይ እየመከረ ነው
የፕላን በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በ2016 ረቂቅ በጀት ላይ በቋሚ ኮሚቴውና ከህዝብ የተነሱ ጥያቄዎችን ለምክር ቤቱ አቅርቧል፡፡
ለባለበጀት መስሪያ ቤቶች የተደለደለው በጀት ምን ያክል የተቋማትን የመፈጸም አቅም፣ የስራ ስፋት፣ የተቋሙ የኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፋይዳ እንዲሁም የኦዲት ግኝት መሰረት ያደረ ምደባ ነው የሚሉ ጥያቄዎች በቋሚ ኮሚቴው ተነስተዋል፡፡
“ምን ያክልስ የወጪ ቁጠባንና ውጤትን መሰረት ያደረገ አመዳደብ ነው?” በሚል ማብራሪያ እንዲሰጥበትም ተጠይቋል፡፡
ከዚህ በፊት በጀት ተይዞላቸው የነበሩ የመንገድ ፕሮጀክቶች በጀታቸው በሽግሽግ ተነስቶ ግንባታቸው ተጀምሮ የተቋረጠ እንዲሁም ያልተጀመሩ ፕሮጀክቶች እንዳሉም ተጠቅሷል፡፡
በዚህም የ2016 ረቂቅ በጀት እነዚህን ፕሮጀክቶች ታሳቢ ያደረገ እና ቅድሚያ የሰጠ መሆኑ ተረጋግጧል ወይ? ማብራሪያ ቢሰጥበት የሚሉ ጥያቄዎች ቀርበዋል።