የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር እያንዳንዱን የሀገሪቱን ጥግ ለመሸፈን ያለመ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር እያንዳንዱን የሀገሪቱን ጥግ ለመሸፈን ያለመ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ዛሬ በደቡብ ኦሞ ዞን ኛንጋቶም ወረዳ ዐሻራቸውን አሳርፈዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው÷”ዛሬ በደቡብ ኦሞ ዞንኛንጋቶም ወረዳ ዐሻራችንን አሳርፈናል። “ብለዋል፡፡
“በእንደዚህ ዓይነት አካባቢ የምናደርገው ጥረት የድርቅን ሥጋት ለመከላከል ያለመ ነው” ሲሉም ገልፀዋል።
እነዚህን ተግባራት በማስቀጠል ለምግብነት የሚውሉ ችግኞችን በመትከል ፍሬያማ ውጤት ማግኘት እንችላለንም ነው ያሉት፡፡