ትናንት የተሰጡት የሬሜዲያል ፕሮግራም ፈተናዎች ተሰረዙ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ትናንት የተሰጡት የሬሜዲያል ፕሮግራም ፈተናዎች መሰረዛቸውን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የ2014 ዓ.ም 12ኛ ክፍል ሬሜዲያል ተጠቃሚ ተማሪዎች ፈተና ትናንት ሰኔ 26 ቀን 2015 ዓ.ም በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መሰጠት መጀመሩ ይታወቃል።
ይሁን እንጂ በፈተና ሂደት በተፈጠሩ ችግሮች ምክንያት የትምህርት ሚኒስቴር የሚከተሉትን ውሳኔዎች ማሳለፉን ገልጿል፡፡
1) ሰኔ 26 ቀን 2015 የተሰጡት የሬሜዲያል ፕሮግራም ፈተናዎች ተሰርዘው ተማሪዎች በቀሩት የትምህርት ዓይነቶች ብቻ እንዲመዘኑ
2) ቀደም ብሎ በሁሉም ሬሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ ተማሪዎች ባላቸው ተቋማት ፈተናውን በአንድ ጊዜ ለመስጠት የታቀደው ተሻሽሎ በተለይም ከ150 በላይ የሆኑና ከ200 በላይ ግቢ ያላቸውን የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፈተና ቀርቶ ወደ ፊት በሚወሰን አግባብ ፈተናው በመስከረም ወር 2016 ዓ.ም እንዲሰጥ
3) በመንግስት ተቋማት የሬሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ የሆኑትን ተማሪዎች በተያዘው ፕሮግራም መሰረት እንዲሰጥ ውሳኔ አሳልፏል።