Fana: At a Speed of Life!

ተቋማቱ ሙሥናን ለመዋጋት በጥምረት ሊሠሩ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት እና የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ሙሥናን ለመዋጋት በጋራ መሥራት የሚያስችላቸውን ሥምምነት ተፈራረሙ።

ስምምነቱን የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ዋና ኦዲተር መሰረት ዳምጤ እና የፌዴራል የሥነ-ምግባርና የጸረ-ሙሥና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሳሙኤል ኡርቃቶ (ዶ/ር) ተፈራርመዋል።

በሀገር ደረጃ በሥፋት የሚስተዋለውን ሙሥና እና ብልሹ አሰራር ለመከላከል የጋራ ጥረት የሚጠይቅ በመሆኑ በጥምረት ለመሥራት ሥምምነት ላይ መድረሳቸውም ተመልክቷል፡፡

ተቋማቱ በሚያደርጉት የመረጃ ልውውጥ ከመመሪያና ደንብ ውጭ የሚሰሩ ግለሰቦችና ተቋማትን የመቆጣጠርና የማስተካከያ እርምጃ እንዲወሰድ የማመላከት ሥራ እንደሚሰሩ የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

በሥምምነቱ መሰረት የፌዴራል ዋና ኦዲተር የኦዲት ሪፖርቶችን ለተወካዮች ምክር ቤት ካቀረበ በኋላ ለኮሚሽኑ የሚልክ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.