ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል እና ቀይ ጨረቃ ፌዴሬሽን የአስተዳደር ቦርድ አጥኚ ኮሚቴ አባላት ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲሲ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት እና የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የበላይ ጠባቂ ሣኅለወርቅ ዘውዴ የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል እና ቀይ ጨረቃ ፌዴሬሽን የአስተዳደር ቦርድ አጥኚ ኮሚቴ አባላትን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ፡፡
የኮሚቴ አባላቱ በኢትዮጵያ የሥራ ጉብኝት አድርገዋል፡፡
ከጉብኝታቸው በኋላም ከፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም÷ የኢትዮጵያ ቀይመስቀል ማኅበር እንቅስቃሴዎችን በተመለከተ መክረዋል፡፡
የተጠናከረ ትብብር እና ድጋፍ መደረግ ባለባቸው ጉዳዮች ላይም መወያየታቸውን የፕሬዚዳንት ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡