Fana: At a Speed of Life!

በአዳማ ከተማ የትምህርት ቤቶች አውደ ርዕይ ተከፈተ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል አዳማ ከተማ ለአራት ቀናት የሚቆይ የትምህርት ቤቶች አውደ ርዕይ ዛሬ ተከፍቷል፡፡

አውደርዕዩን የከፈቱት የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) እና የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ናቸው፡፡

አውደ ርዕዩ የተከፈተው በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ግቢ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ባዘጋጀው አውደ ርዕይ ላይ÷ ኢፈ ቦሩ እና ልዩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እየተሳተፉ ነው፡፡

አውደ ርዕዩ ለመጀመሪ ጊዜ የተዘጋጀ ሲሆን÷ በተማሪዎች የተሠሩ የተለያዩ የፈጠራ ሥራዎች ቀርበዋል፡፡

በኢፋ ደለሳ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.