የኢትዮ- ጅቡቲ የሕዝብ ለሕዝብ እና የዲፕሎማሲ ፎረም እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እና ጅቡቲ የሕዝብ ለሕዝብ እና የዲፕሎማሲ ፎረም በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡
በመድረኩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ፣ በጅቡቲ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሲራጅ ኦማር የተመራ ልዑክ እና የኢጋድ ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡
ፎረሙ በኢትዮጵያ እና ጅቡቲ መካከል ያለውን የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ያለመ ነው ተብሏል፡፡
አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ÷ ሀገራት በንግድ፣ ትራንስፖርት፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች የተሳሰሩ መሆናቸውን አውስተዋል፡፡
የሁለቱ ሀገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ታሪካዊ እና በጠንካራ ወዳጅነት ላይ የተመሰረተ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡
በመድረኩ የኢትዮጵያና እና የጅቡቲ ሕዝቦችን ግንኙነት፣ ቀጣናዊ ፍልሰትን፣ የአየር ንብረት ለውጥን እና የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ ተሞክሮን የሚዳስሱ ፅሁፎች ቀርበው ምክክር እንደሚደረግ ተመላክቷል፡፡