Fana: At a Speed of Life!

የዓለም የሠራተኞች ቀን ተከበረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 23፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የዓለም የሠራተኞች ቀን በዓለም ለ131ኛ ጊዜ በሀገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ45ኛ ጊዜ ተከበረ ።

ቀኑ በየዓመቱ ሚያዚያ 23 ቀን የሚከበር ሲሆን ሠራተኞች ያደረጉትን ትግል ለማስታወስ የሚከበር ነው።

ዘንድሮ ቀኑ በኢትዮጵያ “ራሳችንን እና ማህበረሰባችንን ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በመጠበቅ ምርታማነትን እናስቀጥላለን”  በሚል መሪ ቃል ነው የተከበረው።

በዓሉ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት እንደወትሮው አደባባይ ተወጥቶ ወይም ተሰባስቦ ሳይሆን ሁሉም በየቤቱ ሆኖ በማሰብ ነው የተከበረው።

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.