Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን ከኢትዮ-ጅቡቲ የህዝብ ለህዝብ ዲፕሎማሲ ልዑክ ጋር አረጓዴ ዐሻራቸውን አኖሩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከኢትዮ-ጅቡቲ የህዝብ ለህዝብ ዲፕሎማሲ ልዑክ ጋር በመሆን በአይ ሲ ቲ ፓርክ አረንጓዴ ዐሻራቸውን አኑረዋል፡፡

አቶ ደመቀ በወቅቱ ባደረጉት ንግግር÷ ጅቡቲን በአረንጓዴ ዐሻራ ማሳተፍ ዘርፈ ብዙ የጋራ ጥቅም እንዳለው ተናግረዋል፡፡

ዓለምን እየፈተነ ላለው በረሃማነት መፍትሔ ሊሆን የሚችለው አረንጓዴ ዐሻራ መሆኑን ገልጸው ለዚህም ኢትዮጵያ የጀመረችውን የአረንጓዴ ዐሻራ ሥራ የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት እንደልምድ እየወሰዱት መሆኑን አመልክተዋል፡፡

ይህም ለእርስ በርስ ግንኙነት እና ለስኬታማ የአረንጓዴ ዐሻራ ዲፕሎማሲ የራሱን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክተ ነው የገለጹት፡፡

በዚሁ ዘርፍ ጅቡቲ ከኢትዮጵያ ጋር የሚደነቅ ስራ እየሠራች መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የሁለቱ ሀገራት ዘርፈ ብዙ ግንኙነትም ይበልጥ ሊጠናከር እንደሚገባው አመላክተው በዛሬው ዕለት በአይ ሲ ቲ ፓርክ የአረንጓዴ ዐሻራቸውን በጋራ ማስቀመጣቸው  ግንኙነታቸውን ከማጠናከር ባሻገር ለትውልድ የሚሸጋገር ተግባር ነው ብለዋል፡፡

በአዲስ ታምራት

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.