Fana: At a Speed of Life!

አስተዳደሩ ሄልቬታስ ስዊስ ኢንተር ኮፕሬሽን  ከተባለ አለም አቀፍ ድርጅት ጋር ስምምነት ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ሄልቬታስ ስዊስ ኢንተር ኮፐሬሽን ከተባለ ዓለም አቀፍ ድርጅት ጋር ተንጠልጣይ የእግረኛ መሻገሪያ ድልድዮችን ለመገንባት የሚያስችል የትብብር መግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል፡፡

በድርጅቱ አማካኝነት ባለፉት 20 ዓመታት በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ከ110 በላይ ተንጠልጣይ የእግረኛ መሻገሪያ ድልድዮች ተገንብተው ለአገልግሎት መብቃታቸው ተገልጿል፡፡

ተንጠልጣይ የእግረኛ መሻገሪያ ድልድዮች ፕሮግራም ዙሪያ ጥምጥም ጉዞዎችን ለማስቀረት የሚያስችል እና የማህበረሰቡን የመዳረሻ ችግር በእጅጉ የሚቀርፍ ፕሮግራም ነው፡፡

በዛሬው ዕለት የተፈረመው ሰነድም በሚቀጥሉት ጥቂት ዓመታት በተለያዩ አካባቢዎች ተንጠልጣይ የእግረኛ መሻገሪያ ድልድዮችን በስፋት ለመገንባት የሚያስችል መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

ፕሮግራሙን ለማስፈፀም የሚያስፈልገው ገንዘብ በዋናነት በኢትዮጵያ መንግስት እና በሄልቬታስ ስዊስ ትብብር የሚሸፈን መሆኑን የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.