Fana: At a Speed of Life!

ናሚቢያ የዲጅታል ግብይትን የሚቆጣጠር ህግ አፀደቀች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ናሚቢያ የዲጅታል ግብይትን (ክሪፕቶከረንሲን) የሚቆጣጠር ህግ በብሄራዊ ምክር ቤቷ ማፅደቋን አስታውቃለች፡፡

ውሳኔው በሀገሪቱ የሚፈፀሙትን  የዲጅታል ግብይቶች በህግ ማዕቀፍ ውስጥ በማካተት  ህጋዊ መሰረት ለማስያዝ  እና ለመቆጣጠር ያለመ ስለመሆኑ ነው የተገለፀው፡፡

በተያዘው ወር የፀደቀው ይህ ህግ የዲጅታል ንብረቶችን፣ ምስጢራዊ የገንዘብ ምንዛሬዎችን እንዲሁም የዲጅታል ግብይት አገልግሎት ሰጭዎችን ይቆጣጠራል የተባለ ሲሆን ለሀገሪቱ የፋይናንስ ኢንዱስትሪ በጎ ጎን እንዳለው ተመላክቷል፡፡

ህጉ ተግባራዊ ሲሆን ናሚቢያ የዲጅታል ግብይቶችን ተግባር እና ሃላፊነታቸውን የሚቆጣጠር መስሪያ ቤት እንደምታቋቁም ተገልጿል፡፡

ህጉ የሸማቹን ህብረተሰብ ጥበቃ ለማረጋገጥ፣ ያለአግባብ  የሚደረግ ግብይትን መቆጣጠርን ጨምሮ ህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውርን ለመግታት፣ ለሽበርተኞች የሚውለውን የገንዘብ ድጋፍ ለመቆጣጠር እገዛ እንደሚያደርግ የሚጠበቅ መሆኑን ኮይን ቴሌግራፍ አስነብቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.