በግብጽ ሲናይ በረሃ በተፈጸመ ጥቃት 10 ወታደሮች ተገደሉ
አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 23 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በግብጽ ሲናይ በረሃ በተፈጸመ ጥቃት 10 ወታደሮች መገደላቸው ተሰማ።
የሃገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ታመር አል ሪፋይ እንዳሉት ጥቃቱ በደቡባዊቷ ቤር አል አቤድ ከተማ በወታደራዊ ተሽከርካሪ ላይ የተፈጸመ የቦምብ ጥቃት የደረሰ ነው።
በጥቃቱ ከሞቱት በተጨማሪ ቁጥራቸው ያልታወቀ ወታደሮች መቁሰላቸውም ተነግሯል።
እስካሁን ለጥቃቱ ሃላፊነቱን የወሰደ አካል የለም።
በሲና በረሃ የግብጽ የፀጥታ ሃይሎች በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎችን ለማስወገድ ተደጋጋሚ ዘመቻዎች አካሂደዋል።
በዚህ ሂደት 845 ታጣቂዎች እና ከ60 በላይ የፀጥታ ሃይሎች ለህልፈት መዳረጋቸው ይነገራል።
ምንጭ፦ አልጀዚራ
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።