Fana: At a Speed of Life!

የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመከላከል በተቋቋመው ብሔራዊ የሚኒስትሮች ኮሚቴ በእስካሁን አፈፃፀም ላይ ግምገማ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 23፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመከላከል የተቋቋመው ብሔራዊ የሚኒስትሮች ኮሚቴ የእስካሁን አፈፃፀም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት ተገምግሟል።

ግምገማውን በማስመልከት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በፌስ ቡክ ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ የተቋቋመው የሚኒስቴሮች ኮሚቴ በውጤታማነት ሥራውን ሲከውን ቆይቷል ብለዋል።

ሥራዎችም በጥሩ ሁኔታ እየተካሄዱ እንደሆነ መረዳት ተችሏልም ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

እንዲሁም በዚህ ወቅት ያገኘናቸውን መልካም ተሞክሮዎች ተቋማዊ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።

ከሎጂስቲክስ እና ከኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ የፈጠራ ሥራዎች አንጻርም አዳዲስ ምዕራፎች ተከፍተዋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እነዚህን አቅሞች ማጠናከር ከኮቪድ19 በኋላ የተሻለ ዕድገት እንዲኖረን እንደሚያግዝ ገልፀዋል።

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.