Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ዓለም አቀፋዊነት ፎረም ምስረታ ላይ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 23 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዓለም አቀፋዊነት ላይ የሚሰራ ፎረም ለመመስረት በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ ውይይት ተካሄደ።

ውይይቱን የከፈቱት የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ በከፍተኛ ትምህርት ዓለም አቀፋዊነት ዙሪያ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ከዓለም አቀፍ፣ ቀጠናዊ እና ሃገራዊ ምልከታዎች ጋር አያይዘው አቅርበዋል።

ፕሮፌሰር አፈወርቅ ፎረሙን ለማቋቋም ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ያለውን ቁርጠኝነት ገልፀው በቀጣይ ሂደቶች ላይም አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል።

በውይይቱ በዓለም አቀፋዊነት ላይ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እየተከናወኑ ያሉ የፖሊሲ እና ስትራቴጂ የማርቀቅ ስራዎች ያሉበት ሁኔታም ቀርቧል።

በውይይቱ ቀጣይ ስራዎችን በመለየት እና ለታቀዱ ስራዎች ማጠናቀቂያ የጊዜ ገደብ በማስቀመጥ የተጠናቀቀ ሲሆን በፎረሙ ምስረታ፣ በመጠናቀቅ ላይ ያሉት የፖሊሲ እና ስትራቴጂ ሰነዶችን በውይይት አዳብሮ በማጽደቅ እና በከፍተኛ ትምህርት ዓለም አቀፋዊነት ላይ የግንዛቤ ማሳደግ ስራዎች ቅድሚያ ተሰጥቷቸው እንደሚሰሩ ተገልጿል።

የአዲስ አበባ፣ ሃዋሳ፣ መቐለ፣ ጅማ፣ ጅግጅጋ፣ ባህርዳር እና ሰመራ ዩኒቨርሲቲዎች የዓለም አቀፍ ቢሮ ዳይሬክተሮች እና አመራር አባላት፣ የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት እና ምክትል ፕሬዚዳንት እንዲሁም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዚዳንት መሳተፋቸውን ከሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.