Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል ሲሰጥ የነበረው የ8ኛ ክፍል ፈተና ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30 ቀን፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል ሲሰጥ የነበረው የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና መጠናቀቁን የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።

የቢሮው ሃላፊ ኪሮስ ጉዕሽ (ዶ/ር) እንደገለፁት÷ ከሰኔ 28 እስከ ሰኔ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ለተከታታይ ሶስት ቀናት ሲሰጥ የነበረው የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ተጠናቅቋል።

ሃላፊው የፈተና ሒደቱ በስኬት እንዲጠናቀቅ አስተዋፅኦ ላበረከቱ መምህራን፣ የትምህርት አመራሮች ፣ የፀጥታ አካላት እና ወላጆች ምስጋና አቅርበዋል።

ፈተናው የመማር ማስተማር ሒደት በተከናወነባቸው በ75 ወረዳዎች በሚገኙ 1 ሺህ 7 ትምህርት ቤቶች መሰጠቱን የቢሮው መረጃ ያመላክታል፡፡

በተለያዩ ምክንያቶች ፈተናውን ያልወሰዱ ተማሪዎች በሚቀጥለው ዓመት መውሰድ እንደሚችሉ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር አጠቃላይ የትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ኤጀንሲ መግለጹ ይታወሳል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.