Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ከ11 ኪሎ ሜትር በላይ የከፍተኛ ውሃ መስመር ዝርጋታ ተካሂዷል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2015 በጀት ዓመት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 11 ነጥብ 4 ኪሎ ሜትር የከፍተኛ ውሃ መስመር ዝርጋታ መካሄዱን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

 

ሶስተኛው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ሁለተኛ ዓመት የስራ ዘመን አራተኛ እና የበጀት ዓመቱ ማጠቃለያ መደበኛ ስብሰባ ላይ የአስተዳደሩን የ2015 በጀት ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡት ከንቲባዋ እንደገለጹት፥ የመዲናዋ የውሃ የአቅርቦት ፍላጎት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ ተጨማሪ አዳዲስ ፕሮጀክቶችን መቅረፅ ያስፈልጋል።

 

ከገጸ-ምድር እና ከርሠ-ምድር ውሃ መገኛዎች 220 ሚሊየን ሜትር ኪዩብ ውሃ ለማምረት እና ለማሠራጨት ታቅዶ 186 ነጥብ 52 ሚሊየን ሜትር ኪዩብ ውሃ በማምረት ማሰራጨት እንደተቻለ ገልጸዋል።

 

11 ኪሎ ሜትር የከፍተኛ ውሃ መስመር ዝርጋታ ለማካሄድ ታቅዶም ከዕቅድ በላይ ማሳካት መቻሉን ተናግረዋል።

 

በተጨማሪም 141 ነጥብ 3 ኪሎ ሜትር የመለስተኛ መስመር ዝርጋታ መካሄዱንም ጠቁመዋል።

 

የፍሳሽ ቆሻሻ የማንሳት እና የማጣራት አቅምን ለማሳደግ በተሰራው ስራም 165 ነጥብ 48 ኪሎ ሜትር የፍሳሽ መስመር ዝርጋታ ጥናት እና ዲዛይን መካሄዱን አመላክተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.