ተቋማትና ድርጅቶች ለገበታ ለትውልድ የሚያደርጉትን ድጋፍ እንደቀጠሉ ነው
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ተቋማትና ድርጅቶች ለገበታ ለትውልድ የሚያደርጉትን ድጋፍ እንደቀጠሉ ነው።
በ16ኛው ዙር የተለያዩ ተቋማት ከ76 ሚሊየን ብር በላይ ለገበታ ለትውልድ ድጋፍ ማድረጋቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።
በዚህም የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን 30 ሚሊየን ብር፣ የፔትሮሊየም አቅራቢ 26 ሚሊየን 822 ሺህ 668 ብር፣ መኪያ ኢንተርፕራይዝ 10 ሚሊየን ብር፣ የኬሚካል ኢንዱስትሪያል ኮርፖሬሽን 6 ሚሊየን 432 ሺህ 335 ብር እንዲሁም ጌቱ ገለጠ 5 ሚሊየን ብር ለገበታ ለትውልድ ለገሰዋል።