Fana: At a Speed of Life!

የጃፓን ባለሐብቶች መዋዕለ-ንዋያቸውን በኢትዮጵያ እንዲያፈሱ ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጃፓን ባለሐብቶች እና ኩባንያዎች በኢትዮጵያ መዋዕለ-ንዋያቸውን እንዲያፈሱ በጃፓን የኢትዮጵያ አምባሳደር ዳባ ደበሌ ጥሪ አቀረቡ፡፡

የጃፓን ኤምባሲ “ኢንስፓየር አፍሪካ” ከተሰኘ ማኅበር ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ ያሉ ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጮች ፣ ዐቅሞችና አስቻይ ሁኔታዎችን የማስተዋወቂያ መድረክ አካሂዷል።

በመድረኩ ከተለያዩ ከጃፓን ኩባንያዎች የተውጣጡ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል፡፡

አምባሳደር ዳባ ደበሌ÷በኢትዮጵያ ባሉ የኢንቨስትመንት ዕድሎች፣ ለውጭ ገበያ ተመራጭ በሆኑ የግብርና ምርቶች እንዲሁም የቱሪዝም መስኅቦች ላይ ለተሳታፊዎቹ ገለፃ አድርገዋል።

መንግስት ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ማካሄዱንም ለተሳታፊዎቹ አስረድተዋል፡፡

የጃፓን ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ያሉትን የኢንቨስትመንት አማራጮች እንዲቃኙ እና በዕድሎቹ እንዲጠቀሙ እንዲሁም የቱሪስት መዳረሻዎችን እንዲጎበኙም ጥሪ አቅርበውላቸዋል።

በመድረኩ የኢትዮጵያ ባሕላዊ የቡና አፈላልንና ምግቦች ለተሳታፊዎች ማስተዋወቅ መቻሉን በጃፓን የኢትጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.