አየርመንገዱ ከእንግሊዙ የአውሮፕላን ሞተር አምራች ኩባንያ ጋር ስምምነት ተፈራረመ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከእንግሊዙ ሮልስ ሮይስ የአውሮፕላን ሞተር አምራች ኩባንያ ጋር ስምምነት ተፈራርሟል፡፡
ስምምነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቀጣይ ለሚረከባቸው ኤርባስ A350-1000 አውሮፕላን ሞዴል ሞተሮች አጠቃላይ የሰርቪስ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል መሆኑ ተመላክቷል፡፡
ኮንትራቱ የተፈረመው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የስራ ሃላፊዎች በእንግሊዝ ደርቢ የሚገኘውን የሮልስ ሮይስ የአውሮፕላን ሞተር አምራች ኩባንያ ዋና መሥሪያ ቤት በጎበኙበት ወቅት ነው ።
በተያያዘም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ እንግሊዝ የመጀመሪያ በረራ የጀመረበትን 50ኛ ዓመት እያከበረ እንደሚገኝ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡