Fana: At a Speed of Life!

አቶ ኦርዲን በድሪ ከሀረሪ ክልል ዳያስፖራዎች ጋር  ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኦርዲን በድሪ ከተለያዩ የአለም ሀገራት ከተውጣጡ የሀረሪ ዳያስፖራዎች ጋር በካናዳ ቶሮንቶ  ተወያይተዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ኦርዲን በድሪ ÷ውይይቱ በርካታ ብዥታዎችን ያጠራንበት እና በዋና ዋና ሀገራዊ እና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት የተፈጠረበት ነው ብለዋል።

በተለይም ችግሮችን ከዳያስፖራው ጋር በቅንጅት በመፍታት በቀጣይም ዳያስፖራው በክልላዊ እና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ርብርብ ይደረጋል ማለታቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ ለ25ኛው ጊዜ እየተከበረ ለሚገኘው አለም አቀፍ የሀረሪ ባህል እና ስፖርት ፌስቲቫል ስኬታማነት ድጋፍ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.