የፌዴራል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ከተለያዩ ክልሎች የካቢኔ አባላት ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በክረምት በሚከናወኑ ዘርፈ-ብዙ የልማት ሥራዎች ዙሪያ ከሐረሪ፣ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦችና ሲዳማ ክልሎች የካቢኔ አባላት ጋር ምክክር አካሄዱ፡፡
ውይይቱ በዋናነት በክረምቱ ወራት በሚተገበሩ እና በተመረጡ የትኩረት መስኮች ላይ መሠረት ያደረገ ስለመሆኑ ተጠቁሟል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ሰሞኑን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሰጡት ማብራሪያ ከሐምሌ 1 ቀን 2015ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ አስር ቀናት ሁሉም ሚኒስትሮችና ሚኒስትር ዴዔታዎች በየክልሉ የስራ ግምገማ ያደርጋሉ ማለታቸው ይታወሳል።
በሰላም ሚኒስትር ብናልፍ አንዷለም፣ በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ እና በትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር)ና ሌሎች ሚኒስትር ዴዔታዎችን ያካተተ ቡድን በሐረሪ፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች እና ሲዳማ ክልሎች በመገኘት ከክልሉ ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡
ልዑኩ በክረምት የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት፣የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር፣የሌማት ትሩፋት እንቅስቃሴዎችን መገምገም መጀመሩ ተመላክቷል፡፡
በተጨማሪም የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች እንዲሁም ሌሎች የልማት ስራዎች ላይ ድጋፍና ክትትል የማድረግ ተግባራዊ እንቅስቃሴ መጀመሩ ተገልጿል፡፡
በቢቂላ ቱፋ፣ ተጨማሪ መረጃ ከየክልሎቹ ኮሙኒኬሽን