በዱራሜ ከተማ ከ100 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው ፕሮጀክቶች ተመረቁ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በከምባታ ጠምባሮ ዞን ዱራሜ ከተማ ከ100 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው ፕሮጀክቶች ተመርቀዋል፡፡
ዛሬ ለምርቃ የበቁት ፕሮጀክቶች የሕዝብ መድኃኒት ቤት፣ የእሳት አደጋ መከላከያ፣ ለወጣቶች የሚተላለፉ የንግድ ቤቶች፣ የከንባታ ማኅበረሰብ ቴሌቪዥን ጣቢያ እና አደባባይ መሆናቸው ተገልጿል።
በምርቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የደቡብ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ሰርሞሎ ÷የህዝቡ የመልማት ጥያቄን ለመመለስ ዘርፈ ብዙ ጥረት በመደረግ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መለሠ አጭሶ በበኩላቸው÷ከ100 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው መሰረተ ልማቶች አጠናቆ ከማስመረቅ ባለፈ አዳዲስ የልማት ስራዎችን በቀጣይ ለማከናወን መወጠኑን ገልፀዋል ።
ከፕሮጀክቶች ምርቃት ባሻገር አዳዲስ ፕሮጀክቶችን ለመጀመር የሚያስችል የመሠረተ ድንጋይ መቀመጡ ተመላክቷል፡፡
በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ የፌደራል፣ የክልልና የዞን ከፍተኛ አመራሮችና ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል ።
በብርሃኑ በጋሻው