Fana: At a Speed of Life!

ከጥቃቅን ወደ መካከለኛ ለተሸጋገሩ 377 ስራ ፈጣሪዎች እውቅና ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከጥቃቅን ወደ መካከለኛ ለተሸጋገሩ 377 ስራ ፈጣሪዎች እና 60 የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ ባለሙያዎች እውቅና እና ሽልማት ተሰጥቷቸዋል፡፡

እውቅና የተሰጣቸው ኢንተርፕራይዞች በስራቸው ከ5 ሺህ በላይ ለሆኑ ወጣቶች የስራ እድልን የፈጠሩ ናቸው ተብሏል፡፡

የአንድ ማዕከል አገልግሎት ባለሙያዎች ደግሞ ለማዕከሉ ውጤታማ ስራ የተሻለ አፈጻጸም ያስመዘገቡ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

የዕውቅና መርሐ ግብሩ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ደመቀ መኮንን፣ የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል እና የአፍሪካ የኤሌክትሮኒክስ ንግድ ቡድን የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት ተካሂዷል።

ዛሬ ከጥቃቅን ወደ መካከለኛ የተሸጋገሩት ኢንተርፕራይዞች በአፈጻጸም ጥራታቸው እና በስራ ፈጠራ ልኬት ውጤታማ የሆኑ ናቸውም ተብሏል።

አሁን ላይ በሃገር ደረጃ ከ2 ሚሊየን በላይ ኢንተርፕራይዞች ወደ ስራ በመግባት ለሃገር ኢኮኖሚ የበኩላቸውን እየተወጡ መሆኑም ተመላክቷል፡፡

በይስማው አደራው

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.