ስፓርት

500 ስፖርተኞች የሚሳተፉበት የክለቦች ሻምፒዮና ተጀመረ

By ዮሐንስ ደርበው

July 10, 2023

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ የወርልድ ቴኳንዶ ፌዴሬሽን የ2015 ዓ.ም የክለቦች ሻምፒዮና ውድድር በአራት ኪሎ ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል ተጀምሯል።

በሻምፒዮና ውድድሩ 45 ክለቦች በ12 የኪሎ ካታጎሪ በሁለቱም ጾታ ይወዳደራሉ፡፡

በአጠቃላይ 500 ስፖርተኞች በውድድሩ እንደሚሳተፉ አዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

የ2015 ዓ.ም የአዲስ አበባ የወርልድ ቴኳንዶ የክለቦች ሻምፒዮና ውድድር ሐምሌ 5 ቀን 2015ዓ.ም ፍፃሜውን ያገኛል።