ጨፌ ኦሮሚያ 5ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሔድ ጀመረ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጨፌ ኦሮሚያ 6ኛ የስራ ዘመን ሁለተኛ ዓመት 5ኛ መደበኛ ጉባኤ በአዳማ ከተማ መካሔድ ጀምሯል፡፡
ለሁለት ቀናት በሚካሄደው ጉባዔ÷የተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ውይይት ተደርጎ ውሳኔዎች ይተላለፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የበጀት ዓመቱ የክልሉ መንግስት አፈፃፀም ሪፖርት እና ቀጣይ ዕቅድ ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግበትም ተጠቁሟል፡፡
የበጀት አጠቃቀም፣ የሰላም እና የፀጥታ ጉዳይ፣ የዜግነት አገልግሎት፣ የልማት ስራዎች እና የህዝቡ ተደጋጋሚ ጥያቄ የሆነው የመልካም አስተዳደር እንዲሁም የአገልግሎት አሰጣጥ ቀዳሚ የውይይት ርዕሶች እንደሚሆኑም ተገልጿል፡፡
በተጨማሪም ጉባዔው በሁለት ቀናት ቆይታው ሁለት ረቂቅ አዋጆችን ተወያይቶ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
ረቂቅ አዋጆቹም÷የ2015 ዓ/ም የበጀት ዓመት ተጨማሪ በጀት እና የ2016 ዓ/ም በጀት ዓመት ረቂቅ አዋጆች መሆናቸውን በመግለጫው ተጠቅሷል፡፡