በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የመውጫ ፈተና እየተሰጠ ነው
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ስ) በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የ2015 ዓ.ም የተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና መሠጠት ጀምሯል፡፡
በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ከስድስት ኮሌጆች የተውጣጡ 917 ተማሪዎች የመውጫ ፈተና እየወሰዱ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በተጨማሪም ከግል ኮሌጆች የተውጣጡ ከ800 በላይ ተማሪዎች የመውጫ ፈተናውን መውሰድ መጀመራቸውን የዩኒቨርሲቲው መረጃ ያመላክታል፡፡
በተመሳሳይ የአሶሳ ዩነቨርሲቲ በተያዘው መርሐ ግብር መሠረት ለመደበኛ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና በኦንላይን እየሰጠ ነው፡፡
እንዲሁም በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዘንድሮ የሚመረቁ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና እየወሰዱ ነው፡፡
በሌሎች የትምህርት ዘርፎች የሚመረቁት ደግሞ ዛሬ የመውጫ ፈተና እየወሰዱ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው መረጃ ያመላክታል፡፡
ዩኒቨርሲቲው በመደበኛ፣ በክረምትና በዕረፍት ቀናት ያስተማራቸውን 2 ሺህ 750 ተመራቂ ተማሪዎች ለመውጫ ፈተናው ያዘጋጀ ሲሆን፤ በአጠቃላይ ከተለያዩ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመጡትን ጨምሮ ከ12 ሺህ 000 በላይ ተፈታኞች በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተና እንደሚወስዱ ተገልጿል፡፡