Fana: At a Speed of Life!

ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሰዓሊ ጁሊ ምህረቱ አዲሱን የቢ ኤም ደብሊው መኪና እንድታስውብ ተመረጠች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአብስትራክት ስዕሎቿ የምትታወቀው ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ጁሊ ምህረቱ አዲሱን የቢ ኤም ደብሊው መኪና በስዕል እንድታስውብ ተመርጣለች፡፡

ሰዓሊዋ የቢ ኤም ደብሊው የዲዛይን ፕሮጀክትን በሚመሩት የዓለም አቀፍ የሙዚየም ዳይሬክተሮች እና ተቆጣጣሪ ዳኞች ነው የመኪናውን ዲዛይን ለመስራት የተመረጠችው፡፡

በዚህም መሰረት በአርቲስት ጁሊ ምህረቱ ስራዎች የሚያሸበርቀው የ’ቢ ኤም ደብሊው ኤም ሃይብሪድ ቪ8’ መኪና በሰኔ ወር 2024 በሚካሄደው የ’24 ሰአት ሌ ማንስ ውድድር’ ላይ ይቀርባል ነው የተባለው፡፡

አርቲስቷ በስራዎቿ በርካታ እውቅና እና ሽልማቶችን ያገኘች ሲሆን በአሜሪካ በ2005 እና 2015 የተዘጋጀውን የማክ አርቱር ህብረት አዋርድን አሸንፋለች፡፡

በተጨማሪም  በፈረንጆቹ 2015 የአሜሪካ የሥነጥበብ ሜዳሊያ ሽልማትን እንዲሁም በ2007 የበርሊን ፕራይዝ ሽልማትን ያሸነፈችማሸነፍ ችላለች።

በተጨማሪም በፈረንጆቹ 2021 የአሜሪካ የሥነጥበብ እና ሳይንስ አካዳሚ እና የብሔራዊ ዲዛይን አካዳሚ አባል በመሆን ተመርጣለች።

አርቲስት ጁሊ ምህረቱ ከኢትዮጵያዊ አባቷ እና ከአሜሪካዊ እናቷ በአዲስ አበባ መወለዷን ከኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.