ሽሮ ሜዳ አካባቢ ዘመናዊ የዕደጥበብ ንግድ ማእከል እየተገነባ እንደሚገኝ ተገለፀ
አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 24 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ)ሽሮ ሜዳ አካባቢ ዘመናዊ የዕደጥበብ ንግድ ማእከል ( የማምረቻ እና መሸጫ) እየተገነባ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ።
ኢትዮጵያ የምትታወቅበት የሸማ እና የእደ ጥበብም የንግድ ስርአቱ ዘመናዊ መልክ እንዲኖረው የሚስችል ማዕከል መሆኑን ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ ገልፀዋል።
የማእከሉን ግንባታ በፍጥነት በማጠናቀቅ በአካባቢው የሚገኙ ሌሎች የንግድ ቦታዎችንም በዘመናዊ መልኩ እንደሚገኑ ነው የተናገሩት።
ከዚህ ባለፈ በአካባቢያቸው በግንባታ ላይ የሚገኘው ደረጃውን የጠበቀ መንገድም በመጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ ተጠቁሟል።