ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ለአፍሪካ የተቋም መሪዎች የሚሰጠውን ልዩ ሽልማት ለመቀበል ወደ እንግሊዝ አቀኑ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ለአፍሪካ የተቋም መሪዎች የሚሰጠውን ልዩ ሽልማት ለመቀበል ወደ እንግሊዝ አቀኑ፡፡
ሽልማቱን ያዘጋጀው ጠንካራ ተቋማት በመገንባት አርአያነት ያለው ስራ ላከናወኑ መሪዎች ዓለም ዓቀፍዊ እውቅናና ሽልማት የሚሰጠው ታዋቂው የአፍሪካ ሊደርሽፕ መፅሄት ነው፡፡
ኮሚሽነር ደበሌ ባለፈው የበጀት ዓመት “የአፍሪካ ምርጡ የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር” ተብለው በጋና ዋና ከተማ አክራ መሸለማቸውን ከጉምሩክ ኮሚሽን ያገኘነው መረጀ ያመላክታል፡፡