Fana: At a Speed of Life!

ማኅበሩ ለሱዳን ስደተኞች ከ10 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 3 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ለሱዳን ስደተኞች እስከአሁን 10 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ድጋፍ ማድረጉን ገለጸ፡፡

ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀልና የቀይ ጨረቃ ፌደሬሽን አስተዳደር ሰሞኑን በተለያዩ መጠለያ ጣቢያዎች ያደረጉትን ጉብኝት አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር  ጋር በመሆን ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በመግለጫቸውም÷ በሱዳን በተቀሰቀሰው ግጭት ምክንያት 57 ሺህ 500 ስደተኞች በመተማ እንዲሁም 18 ሺህ 223 በኩርሙክ መጠለያ ጣብያ እንዳሉ  ገልጸዋል፡፡

ማኅበሩም በመጠለያ ጣብያዎቹ ለሚገኙ ስደተኞች÷ አልሚ ምግቦች፣ የንጽሕና መጠበቂያ ቁሳቁስ፣ የአምቡላንስ፣ ቤተሰብን የማገናኘት እና የመጠለያ አገልግሎቶችን እየሠጠ መሆኑ ተብራርቷል፡፡

የዓለምአቀፍ ቀይመስቀልና ቀይ ጨረቃ ፌደሬሽን ኃላፊ ዣቪር ካስቴላኖስ÷ የኢትየጵያ ሕዝብ ለስደተኞቹ ሰብዓዊነት የተሞላበት ድጋፍ እያደረገ ስለመሆኑ በጉብኝቴ ወቅት ተመልክቻለሁ ብለዋል፡፡

ፌደሬሽኑ ከማኅበሩ ጋር በመሆን የሚታዩ ችግሮችን ለመቅረፍ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል፡፡

በታሪኩ ወልደሰንበት

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.