Fana: At a Speed of Life!

በክልሉ በአንድ ጀምበር 20 ሚሊየን ችግኝ ለመትከል ዝግጅት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል “ነገን ዛሬ እንትከል” በሚል መሪ ሐሳብ የፊታችን ሰኞ በአንድ ጀምበር 20 ሚሊየን ችግኝ ለመትከል ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁ ተገለጸ፡፡

በክልሉ የሚከናወነው የችግኝ ተከላ እንደሀገር ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓ.ም 500 ሚሊየን ችግኞችን በአንድ ጀምበር ለመትከል የተያዘው ሀገራዊ የአረንጓዴ ዐሻራ ንቅናቄ አካል መሆኑ ተገልጿል፡፡

ባለፉት አራት ዓመታት 646 ሚሊየን 499 ሺህ 415 ችግኞች በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መተከላቸውን ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡

የክልሉ ሕዝብ፣የሐይማኖት ተቋማት፣ መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት ሰኞ ለሚከናወነው ታሪካዊ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ስኬት ዐሻራቸውን እንዲያሳርፉ የክልሉ መንግሥት ጥሪ አቅርቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.