Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ የአጎዋ ዕድል ተጠቃሚነት እንዲታደስ የአሜሪካ የአልባሳት ማኅበር ጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የአጎዋ ዕድል ተጠቃሚነት እንዲታደስ የአሜሪካ የአልባሳት ማኅበር ጠየቀ፡፡

የአፍሪካን የማደግ ዕድል ለማፋጠን የተፈቀደው የ”አጎዋ” ዕድል የተጠቃሚነት ቢያንስ ለቀጣዮቹ አሥርት ዓመታት እንዲራዘም ማኅበሩ ጠይቋል፡፡

ዕድሉ ለአሥር እና ከዛ በላይ ዓመታት የሚራዘም ከሆነ የአሜሪካ ባለሐብቶች በአኅጉሩ በኢንዱስትሪው ዘርፍ ያለውን የሥራ አማራጮች ለመዳሰስና እስከ ፈረንጆቹ 2025 ድረስ ባለው የጊዜ ገደብ ተወዳዳሪ ኢንዱስትሪ ለመገንባት ተነሳሽነቱ እንዳላቸው ማኅበሩ ጠቁሟል፡፡

ኢትዮጵያ ከአጎዋ ዕድል ተጠቃሚነት የተሰረዘችው በፈረንጆቹ ጥር 1 ቀን 2022 ሲሆን በሀገሪቷ በሰሜኑ ክፍል ከተከሰተው ግጭት ጋር ተያይዞ በተወሰነ ውሳኔ መሆኑንም ፋይበር ቱ ፋሽን የተሰኘው በአልባሳት እና ፋሽን ላይ መረጃዎችን የሚያጋራ ገጽ አስታውሷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.