Fana: At a Speed of Life!

ኡጋንዳ እንስሳት ልማት ላይ ከኢትዮጵያ ጋር ለመስራት ፍላጎት እንዳላት ገለጸች

በአዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኡጋንዳ ግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ብራይት ረውምሯማ (ዶ/ር) የተመራ ልዑክ ከኢትዮጰያ ግብርና ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ድሪባ ኩማ ጋር ተወያይቷል፡፡

በውይይታቸውም ÷በኢትዮጵያ የእንስሳት የወጪ ንግድ ቁጥጥርና ሰርተፍኬሽን እና አጠቃላይ የእንስሳት ጤና አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት ጋር በተያያዘ ምክክር አድርገዋል፡፡

በግብርና ሚኒስቴር አወቃቀር፣ የእንስሳት ልማት አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ እና የስጋ አምራቾችና ላኪዎችን የአሰራር ሁኔታን የሚዳስሱ ሰነዶች ላይም ውይይት አድርገዋል፡፡

የኡጋንዳ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ብራይት ረውምሯማ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ የእንስሳት ልማት እንቅስቃሴን አድንቀው÷በኢትዮጰያ ያዩትን መልካም ተሞክሮ ከሃገራቸው ነባራዊ ሁኔታ አንፃር ተግባራዊ እንደሚያደርጉም ተናግረዋል፡፡

ሃገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር በእንስሳት ልማት ላይ በጋራ ለመስራት ያላትን ፍላጎትም ሚኒስትር ዴኤታው ገልፀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ድሪባ ኩማ በበኩላቸው÷ልዐካን ቡድኑ የእንስሳት ልማት ላይ ልምድ ለመቅሰም ወደ ኢትዮጵያ በመምጣቱ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡

ልዑካኑ በቆይታቸው ሚሌ እንስሳት ኳራንታይን ጣቢያን፣ ብሄራዊ የእንስሳት ጤና ኢንስቲትዩትን፣ የእንስሳት ልማት ኢንስቲትዩትንና ሞጆ የሚገኙ የኤክስፖርት ቄራ ድርጅቶችን ይጎበኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከግብርና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጀ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.