Fana: At a Speed of Life!

በሶማሌ ክልል የአርብቶ አደሩን ኑሮ ለማሻሻል የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ – አቶ ሙስጠፌ መሃመድ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል የአርብቶ አደሩን ኑሮ በማሻሻል ተፈጥሯዊ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎችን መቋቋም የሚችል ማህበረሰብ ለመፍጠር የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ ገለጹ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ ለሰው ሰራሽ እና ተፈጥሮአዊ አደጋዎች የማይበገር ማህበረሰብ ለመፍጠር በተዘጋጀ የረጅም አመት እቅድ ላይ ከተለያዩ መንግስታዊ ካልሆኑ ተራድኦ ድርጅቶች ጋር በተወያዩበት ወቅት እንደገለጹት÷ የሚያጋጥሙ ሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ አደጋዎችን ለመፍታት እየተሰራ ነው።

በተለይም የህብረተሰቡን ኑሮ ለማሻሻል መንግስት የጤና፣ የትምህርት፣ የመሰረተ ልማት እና የተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮችን ላይ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

የተዘጋጀው እቅድ የአርብቶ አደሩን ኑሮ በማሻሻል ተፈጥሯዊ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎችን መቋቋም የሚችል ማህበረሰብ ለመፍጠር እንዲሆን መስራት ያስፈልጋል ተብሏል፡፡

ተግባራዊ ለማድረግም ከመንግስት፣ ከልማት አጋሮች፣ ከሲቪክ ማህበራት እና ከግሉ ዘርፍ የተቀናጀ ጥረት የሚጠይቅ ነው መባሉን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.