Fana: At a Speed of Life!

በሶማሊያ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 70 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 24 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሊያ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ተጨማሪ 70 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በዚህም በሀገሪቱ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 671 የደረሰ ሲሆን አጠቃላይ በቫይረሱ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች 31 ነው ተብሏል።

በኬንያም በ24 ሰዓታት ውስጥ 1 ሺህ 195 ሰዎች የቫይረሱ ምርመራ ተደርጎላቸው 24 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

በደቡብ ሱዳንም አዲስ 10 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር የገለፀ ሲሆን በዚህም በሀገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ወደ 45 ከፍ ብሏል።

ናይጀሪያም አርብ ዓለት 238 በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን መገኘቱን ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.