ዓለምአቀፋዊ ዜና

በሶማሊያ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 70 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

By Tibebu Kebede

May 02, 2020

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 24 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሊያ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ተጨማሪ 70 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በዚህም በሀገሪቱ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 671 የደረሰ ሲሆን አጠቃላይ በቫይረሱ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች 31 ነው ተብሏል።