Fana: At a Speed of Life!

የአረንጓዴ አሻራ የአካባቢ መራቆትን በማስቀረት ወደ ልማት የሚወስድ አገራዊ አጀንዳ መሆኑ ተመለከተ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር የአካባቢ መራቆትን በማስቀረት ኢትዮጵያን ወደ ልማት የሚወስድ አገራዊ አጀንዳ ነው ሲሉ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀኔራል ተመስገን ጥሩነህ ተናገሩ፡፡

የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት አመራርና እና ሰራተኞች በብሔራዊ መረጃና ደህንነት ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ግቢ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አካሂደዋል፡፡

ዳይሬክተር ጀኔራል ተመስገን ጥሩነህ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት÷ ተቋሙ ሰራተኞቹን በማስተባበር በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከ20 ሺህ በላይ ችግኞችን ለመትከል እቅድ ተይዞ እየተሰራ ነው፡፡

የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ኢትዮጵያን በበጎ መልኩ እየቀየረ መሆኑን ጠቁመው ÷ መርሃ ግብሩ የአካባቢ መራቆትን በማስቀረት ወደ ልማት የሚወስድ አገራዊ አጀንዳ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

በዕለቱ ከችግኝ ተከላ ጎን ለጎንም በኮሌጁ ቅጥር ግቢ ውስጥ እየተከናወኑ ያሉ የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር ስራዎች መጎብኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.